What is Yebbo? When people hear about
the word "Yebbo" the first thing they are asking is what is "Yebbo"? So far
only few people knew what is our "Yebbo" means. As we meet several people
from different parts of the world we have various meanings for "Yebbo". Some
people told us Yebbo is a spear, other told us wild dog, some other people
told us Yebbo is " be happy". We like all the meanings. However the real
name Yebbo comes from a small farm village in Ethiopia. It is where our
ancestors born, lived and had a wonderful time still having a wonderful
time. It is like a place in the movie the Lion King. It is a place "Akum
Metata", a place where "no worries" Yebbo is like an
oasis, like a place where you smell 100% natural organic air.
Where exactly is Yebbo? Well, we tried to point the exact
location of Yebbo in a map but so far it ሰ hard even to find big
Ethiopian cities. However we can tell you approximately where is Yebbo
located.
Yebbo is located in the state of Gojjam, in Debre Markos
Awraja.
It is few miles to south west of city of Debre Markos.
Most of the time people walk to Yebbo. It takes about two hrs of walking. St
Mary (Yebbo Mariam) is the only church in this farm village. The
people are 100% farmers. Every year when the yearly Yebbo's St Mary
(Yebbo Mariam) celebration people from the town and the neighborhood go to
Yebbo. In Yebbo guest is like a king. There is no invitation to be a guest.
During the celebration after the church people can go anybody's house and
eat and drink what every they like. People can go to anyone's
house and eat and drink for free. Nobody asks who you are or where are you
from.
Yebbo's soil is so fertile. people do not wait for the
rainy season to cultivate their crop. instead they use irrigation and Yebbo
is green all years around. Witren river is the main supply of water and
irrigation system. When you go to Yebbo you will smell nature. lemon tree,
coffee tree, orange tree, lavender tree, jasmine tree, wild berry,
strawberry, Shola, choshim, chat, tringo, green paper, mango, tiringo, and
so on.
Yebbo is a paradise. That is where our name comes from
Next time we will have the photo gallery what the actual
Yebbo looks like. What to visit Yebbo? well let us know we can arrange your
trip.
=====================
ለመሆኑ የቦ ምንድን ነው?
እንሆ ዛሬ የየቦን ስም ይዘን ትርጉሙን ሳንነግራችሁ ወደ አስር አመት
ሊጠጋን ነው፡፡ በነዚሁ አመታት ውስጥ ስለ የቦ ያልደረሰን ጥያቄ የለም፡፡ በሪድዮ፣ በቴሌዥን በጋዜጣ፣ ሰወች
በአካል መጥተው፣ በኢሜል እና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሰለየቦ ትርጉም የተጠየቅን ሲሆን፣ የሚገርመው ብዛት ያላቸው ቋንቋች
ለየቦ ትርጉም አላቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ የቦ ማለት ጦር፣ ሀይለኛ ውሻ፣ መደሰት እና የመሳሰሉ ለየቦ የተሰጡ
ትርጎሞች ናቸው፡፡
ዋናው እና ለእኛ የቦ
ለማለት ያስቻለን ስም ግን የመጣው አያት ቅድማያቶቻችን ተወልደው አድገው የተወሰነው ዘር ደግሞ እስከ አሁን ከሚኖርበት
ከተቀደሰው እና ከተባረከው የገጠር መንደር የተወሰደ ነው፡፡ የቦ ወይም
የቦ ማርያም
የሚገኘው በጎጃም ክፍለ ሀገር በደብረማርቆስ አውራጃ ከደብረ ማርቆስ ከተማ በእግር በግምት ወደ ሁለት ሰዓት ከሚወስድ
የገጠር ቦታ ላይ ነው፡፡
የቦ ማለት በምድር ላይ ያለ
ገነት ማለት ነው፡፡እስከ አሁን ድረስ የሚታየኝ የሰው የዋህነት፣ የእንግዳ አክባሪነት፣ እና ትሁትነት ነው፡፡
የቦ እንደሌላው የኢትዮጵያ ገበሬ ዝናብ ጠብቆ የሚያመርት ሳይሆን በመስኖ እየተጠቀመ አመቱ ሙሉ ለምለም የሆነ ቦታ ነው፡፡
ትርንጎ፣ ሎሚ፣ ቡና፣ ሾላ፣ አሽቃሞ፣ ኮሽም፣ ቃሪያ፣ ቲማቲም፣ በሶ ብላ(ዝቃ ቅቤ)፣ ጠጀ ሳር፣ ፊላ፣ ቄጠማ፣ ባኅር
ዛፍ፣ እነጆሪ፣ ዘንባባ፣ እና የመሳሰሉት እፅዋት የተለመዱ ሲሆኑ ገና የውትርንን ወንዝ ተሻግረው ወደ የቦ ሲገቡ
የሚቀበልዎ ሽታ ንፁህ፣ በተፈጥሮ ማእዛ ያማረ ጤናማ አየር ነው፡፡
የቦ ማርያም በያመቱ የሚከበር ታላቅ ንግስ (ባዕል) ነው፡፡ የየቦ ማርያም ቀን ሁሌ
የሚውለው ፍስለታ ከመግባቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ እሁድ ቀን ነው፡፡ በዚህ ባህል ላይ ለመገኘት ከየቦታ ያሉ ምእመናን
ከከተማም ሆነ ከገጠሩ መሄድ የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ቀን ማንም ሰው ከማንም ቤት ከብቶ መብላተም ሆነ መጠጣት መብቱ
ነው፡፡ የሚገርመው የየቦ ሰው በመንገድ ያለፈውን ሰው ሁሉ እረ ባካች ጠበል ቅመሱ እያለ ቤቱ መጋበዙ ነው፡፡ በመቦቴ
አፈር ስሆን እያለ ሰውን ካልበላችሁ ብሎ መለመን የተለመደ ነው፡፡ የቦ አንድን ሰው ሰላም ለማለት ማወቅ አያስፈልገም፡፡
ሰላምታ የእግዚያብሄር ነው ሰለሚባል የተገናኘው ሰው ሁሉ ሰላም ተባባሎ ተሳስቆ ነው የሚለያየው፡፡ ታዲያ የየቦ ማሪያም
ቀን ሁሉም ሰው እኩል ነው፡፡ ሁሉም ሰው በፈለገው ቤት ገብቶ ከፈለገው ጓሮ ሄዶ በልቶ ጠጥቶ ሆዱ ሞልቶ ተደስቶ ለዛሬ
አመት ያድረሰን ብሎ አመስግኖ ነው የሚሄደው፡፡
ያ ነው የኛ የቦ፡፡የምድር ላይ ገነት፡፡ ሰው የሚዋደድበት፣ ሰው የሚፋቀርበት ሰላም እና
ወንድማማችነት የሰፈነበት ቦታ ለመፍጠር፡፡
ታዲያ ያው እንደለመድነው ወደ የቦ ሲመጡ የምንቀበልዎ እንደ እህት እንደ ወንድም፣ እንደ
አባት እንደ እናት አድረገን ነው፡፡
በዚህ አጋጣሚ ይህን ወብሳይት ከዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ በሃሳብም ሆነ በማንኛውም ትብብር
ላደረጋችሁልን ህዝቦች በጣም እናመሰግናለን፡፡ ባጋጣሚ የቦ ከሄዳችሁ የላካችሁ
የቄሰ ገበዝ ዋሲሁን ልጆች ልይሽ ዋሲሁን፣ የደርሰህ ዋሲሁን፣ የ እውነቱ ዋሲሁን፣
የ ሰዋለም ዋሲሁን፣ የታጫውት ዋሲሁን፣ የአንየው ደርሰህ፣ የበቃሉ ደርሰህ የየውብዳር ደርሰህ፣ ዘር ነው በሉ፡፡
ይህም ወብሳት ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት እና ለየቦ ማርያም ህዝቦች ስም የተሰራ ነው፡፡
የቦ፡ የምድር
ላይ ገነት |